በኢፌዲሪ ንግድ ህግ አንቀጽ 366(1)፤367( 1 እና 2) አንቀጽ 372 እና 370 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ
መመስረቻ ጽሁፉ መሰረት የአሸዋ ቴክኖሎጂ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 1ኛ አስቸኳይ እና 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ
ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ፤ም ከጠዋቱ 2፤30 ሰአት ጀምሮ በአዲስ አበባ ኮንቬሽን ሴንተር አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
- ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
1.1 የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ
አ/አ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ቦሌ መድሃኒአለም ሪያሊቲ ህንፃ 9ኛ ፎቅ
ስልክ 0976005100
ድረገጽ www.ashewatechnology.com
1.2 የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር BL/AA/2/0026067/2014
1.3 የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ 277,735,000.00 ብር
1.4 የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) 155,763,250.00 ብር - የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
2.1 የጉባኤውን አጀንዳ ማጽደቅ
2.2 የማህበሩን አመታዊ የክንውን ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ
2.3 የማህበሩን የውጪ ኦዲት ሂሳብ ሪፖርት ማድመጥና ማጽደቅ
2.4 የተቋሙን መተዳደሪያ እና መመስረቻ ፅሁፍ በአዲሱ ንግድ ህግ መሰረት ማሻሻል
3.
1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ
3.1. ቀሪ ክፍያ የጨረሱ ባለ አክሲዮኖች ( የተከፈሉ አክሲዮኖችን ስለማስፈረም)
3.2. አዲስ አባል ስለመቀበል ወይም ያልፈረሙ ባለአክሲዮኖችን ስለማስፈረም - ማሳሰቢያ
3.1 በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻቸውን ስልጣን ባለው የመንግስት አካል
ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ወይም በንግድ ህግ አንቀጽ 377
መሰረት ጉባኤው ከመካሄዱ ከ 3 ቀን በፊት በማህበሩ ዋና መ/ቤት በአካል በመቅረብ ለዚሁ አላማ
በተዘጋጀው የውክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መላክና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ
የጉባኤው ተሳታፊ መሆን የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፤፤
3.2 የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ
ማንነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ
በጉባኤው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ
የዳይሬክተሮች ቦርድ
